Получи случайную криптовалюту за регистрацию!

ነገ 17,154 ትምህርት ቤቶች ይከፈታሉ። ከነገ ጀምሮ ትምህርት የሚጀምሩት በሀገሪቱ ገጠራማ አካ | Educational news

ነገ 17,154 ትምህርት ቤቶች ይከፈታሉ።

ከነገ ጀምሮ ትምህርት የሚጀምሩት በሀገሪቱ ገጠራማ አካባቢ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ናቸው።

ከetv ጋር ቆይታ ያደረጉት በትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች መሻሻል ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት አቶ ዮሀንስ ዎጋሶ 17,154 ትምህርት ቤቶች ነገ ትምህርት ለመጀመር የሚያስፈልጋቸውን ግብዓቶችን አሟልተዋል ብለዋል።

አቶ ዮሀንስ ዎጋሶ ፥ ዝግጅቱን በተመለከተም ነገ የሚከፈቱት ትምህርት ቤቶች አካላዊ ርቀት ለመጠበቅ ምቹ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ እስካሁን 10.7 ሚሊዮን ማስክ የተሰራጨ ሲሆን እንዚህ 17,154 ትምህርት ቤቶች ጋር ማስክ መድረሱን አሳውቀዋል።