Получи случайную криптовалюту за регистрацию!

ቀን 18 / 2 / 2013 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ፈተና | Educational news

ቀን 18 / 2 / 2013 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦን ላይን የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ማካሄድ መጀመሩን አስታወቀ፡፡


የምዝገባ ሂደቱን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ እተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ እንደገለጹት በ2012ዓ.ም በኮቪድ19 ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት በመቃረጡ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ፈተና ወደ ዘንድሮው መተላለፉን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል ፈተና ኦን ላይን ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮም ለዚሁ ቅድመ ዝግጅት ይረዳ ዘንድ ከተመረጡ ትምህርት ቤቶችለተውጣጡ የአይ ሲቲ መምህራንና ለክፍለ ከተማ የፈተና ዝግጅት ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት በዛሬው እለት ወደ ምዝገባ ማስጀመሩን አስታውቀዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም አዲስ አበባ በሚገኙ 143 የመንግስትና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ ጥቅምት 30 ምዝገባው እንደሚካሄድ በመግለጽ ትምህርት ቤቶች መዝጋቢዎቹ ወደየትምህርት ቤቶቻቸው ሲሄዱ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ያሳሰቡ ሲሆን በተለይም ተማሪዎች መዝጋቢዎቹ በሚሄዱበት ቀን መገኘት እንደሚገባቸው አስታውቀዋል፡፡


በአዲስ አበባ ደረጃ በ41 የመፈተኛ ጣቢያዎች ወደ 25,000 የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ተመዝግበው ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚጠበቅ መሆኑንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮም የምዝገባ ሂደቱ እስከሚጠናቀቅ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማቅረብም ሆነ ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንደሚወጣ አቶ ዲናኦል አስረድተዋል፡፡