Получи случайную криптовалюту за регистрацию!

Educational news

Логотип телеграм канала @worldedunews — Educational news E
Логотип телеграм канала @worldedunews — Educational news
Адрес канала: @worldedunews
Категории: Образование
Язык: Русский
Количество подписчиков: 37
Описание канала:

ይህ በአይነቱም ሆነ በይዘቱ አድስ የሆነ ትምህርተዊ መረጃ ብቻ የምናገኝበት ቻነል ነው።
በዚህ ቻናል ከምተገኙት ነገሮች በጥቂቱ. .
♥የትምህርት ሚንስቴር መግለጫ
♥Educational website
♥scholarship info
♥students material
♥teacher's guides
♥reference books
♥fiction books and others
For more info join our channel

Рейтинги и Отзывы

4.00

2 отзыва

Оценить канал worldedunews и оставить отзыв — могут только зарегестрированные пользователи. Все отзывы проходят модерацию.

5 звезд

1

4 звезд

0

3 звезд

1

2 звезд

0

1 звезд

0


Последние сообщения

2021-12-30 13:11:22 The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 11 months. If it remains inactive in the next 30 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
10:11
Открыть/Комментировать
2020-10-30 14:42:43 ቀን 18 / 2 / 2013 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦን ላይን የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ማካሄድ መጀመሩን አስታወቀ፡፡


የምዝገባ ሂደቱን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ እተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ እንደገለጹት በ2012ዓ.ም በኮቪድ19 ወረርሽኝ ምክንያት ትምህርት በመቃረጡ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ፈተና ወደ ዘንድሮው መተላለፉን ተከትሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ የ12ኛ ክፍል ፈተና ኦን ላይን ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮም ለዚሁ ቅድመ ዝግጅት ይረዳ ዘንድ ከተመረጡ ትምህርት ቤቶችለተውጣጡ የአይ ሲቲ መምህራንና ለክፍለ ከተማ የፈተና ዝግጅት ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት በዛሬው እለት ወደ ምዝገባ ማስጀመሩን አስታውቀዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም አዲስ አበባ በሚገኙ 143 የመንግስትና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ ጥቅምት 30 ምዝገባው እንደሚካሄድ በመግለጽ ትምህርት ቤቶች መዝጋቢዎቹ ወደየትምህርት ቤቶቻቸው ሲሄዱ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ያሳሰቡ ሲሆን በተለይም ተማሪዎች መዝጋቢዎቹ በሚሄዱበት ቀን መገኘት እንደሚገባቸው አስታውቀዋል፡፡


በአዲስ አበባ ደረጃ በ41 የመፈተኛ ጣቢያዎች ወደ 25,000 የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ተመዝግበው ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚጠበቅ መሆኑንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮም የምዝገባ ሂደቱ እስከሚጠናቀቅ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማቅረብም ሆነ ሌሎች ድጋፎችን በማድረግ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንደሚወጣ አቶ ዲናኦል አስረድተዋል፡፡
187 views11:42
Открыть/Комментировать
2020-10-19 06:28:55 ነገ 17,154 ትምህርት ቤቶች ይከፈታሉ።

ከነገ ጀምሮ ትምህርት የሚጀምሩት በሀገሪቱ ገጠራማ አካባቢ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ናቸው።

ከetv ጋር ቆይታ ያደረጉት በትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች መሻሻል ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት አቶ ዮሀንስ ዎጋሶ 17,154 ትምህርት ቤቶች ነገ ትምህርት ለመጀመር የሚያስፈልጋቸውን ግብዓቶችን አሟልተዋል ብለዋል።

አቶ ዮሀንስ ዎጋሶ ፥ ዝግጅቱን በተመለከተም ነገ የሚከፈቱት ትምህርት ቤቶች አካላዊ ርቀት ለመጠበቅ ምቹ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ እስካሁን 10.7 ሚሊዮን ማስክ የተሰራጨ ሲሆን እንዚህ 17,154 ትምህርት ቤቶች ጋር ማስክ መድረሱን አሳውቀዋል።
178 views03:28
Открыть/Комментировать
2020-10-17 22:36:21 ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላለፈ መልዕክት

ለክልላችን መምህራን፣የተማሪ ወላጆች፣ ባለሙያዎችና አጋር አካላትና መላ ማህበረሰባችን በሙሉ!!

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሀገራችን ከተከሰተ መጋቢት 2012 ጀምሮ ት/ቤቶች ተዘግተው መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ትምህርት ቤቶችን እንደገና በመክፈት የመማር ማስተማር ስራውን ለማስቀጠል ሀገራዊ ስምምነት ስለተደረሰ ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተቀመጡ ኘሮቶኮሎችን በትምህርት ቤቶች መተግበር የግድ የሚልበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ በዚህም መሰረት፡-

1ኛ.የክልላችን መምህራን፣ የተማሪ ወላጆች፣ ባለሙያዎች፣ አጋር አካላትና ጉዳዩ የሚመለከታችሁ በሙሉ እና በአጠቃላይ የክልላችን ህዝብ ልጆቻችሁ የሚማሩበት ት/ቤት የኮቪድ 19 መከላከል ኘሮቶኮሎችን ለመተግበር የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በጋራ በመረባረብ እንድትፈቱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጥሪውን ያቀርባል፡:

2ኛ. ነባርም ሆነ አዲስ ተማሪዎች፣ የአካባቢው ት/ቤት በሚያወጣው ፣ ኘሮግራም መሰረት በእለቱ በመገኘት ትምህርት እንዲጀምሩ ፣ ወላጆች የበኩላቸውን ኃላፊነት እንድትወጡ እንጠይቃለን፡፡ የ2013 የትምህርት ዘመን በኮቪድ ተፅዕኖ ምክንያት የትምህርት ቀናት አጭር ሊሆኑ ስለሚችሉ አንድም ተማሪ ዘግይቶ ወደ ት/ቤት መግባት ከፍተኛ ጉዳት ያለው መሆኑን ተረድተን ሁላችንም የትምህርት መርሃ ግብሩን አክብረን ለመስራት እንረባረብ !!
ኮቪድን እየተከላከልን 2013 የትምህርት ዘመን ፣የሰላምና የስኬት እንዲሆንላችሁ ቢሮው ምኞቱን ይገልፃል!!
(የአብክመ ትምህርት ቢሮ)

Share join join join
@worldedunews
@worldedunews
@worldedunews
157 views19:36
Открыть/Комментировать
2020-10-14 07:54:14 ቀን 29/ 1 / 2013 ዓ.ም

የእውቅና ፍቃድ የሌላቸዉ እና ህጋዊ ያልሆኑ የርቀት የትምህርት ተቋማት ዝርዝር

1. ፓን አፍሪካ

2. ኢትጲስ

3. አልፋ


4. ሴሌክት

5. ሚሽከን

6. ኬኛ

7. ጅግዳን

8. ሉሲ


t.me/worldedunews

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
139 views04:54
Открыть/Комментировать
2020-10-13 13:41:37
ለትምህርት ቤቶች 50 ሚሊየን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ለማሰራጨት ዝግጅት ተደርጓል- ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ኮሮና ቫይረስ መከላከልን ታሳቢ ያደረገ ትምህርት ለማስጀመር 50 ሚሊየን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ለስርጭት መዘጋጀቱን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። በአፋር ክልል የ2013 ዓ.ም ትምህርት በሚጀመርበት ቅድመ ሁኔታ ላይ የመከረ መድረክ በሰመራ ከተማ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ነቢል መህዲ እንደገለጹት፥ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎቹ…

https://www.fanabc.com/ለትምህርት-ቤቶች-50-ሚሊየን-የአፍና-አፍንጫ/
131 views10:41
Открыть/Комментировать
2020-10-13 13:40:39 አንድ ዴስክ ለአንድ ተማሪ

አቶ አዲሱ አረጋ ትናንት በሰጡት መግለጫ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል፡፡

በአንድ ፈረቃ ከ1 ሺህ በታች ተማሪዎች እንዲማሩ ይደረጋል፣ በአንድ የመማሪያ ክፍል ውስጥም 25 እና ከዛ በታች ተማሪዎች ብቻ ይማራሉ፡፡ አንድ የመማሪያ ዴስክ ለአንድ ተማሪ መሆኑንም ገልጸዋል።

ለሁሉም ተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በነጻ መዘጋጀቱን እና በሁሉም ትምህርት ቤቶች ውሃ የማቅረብ ስራ እንደሚሰራም አስረድተዋል።

ከመምህራን ጋር ተያይዞ እጥረት ሊያጋጥም ስለሚችል በስራ ላይ ያሉ መምህራን ተጨማሪ ክፍሎችን እንዲያስተምሩ ይደረጋል ብለዋል።

በተጨማሪም በጡረታ ለተገለሉ መምህራን እና የመምህርነት ሙያ ኖሯቸው እስካሁን ስራ ላልጀመሩ ወጣቶችም ጥሪ መደረጉንም ገልጸዋል።
(FBC)
@worldedunews
171 views10:40
Открыть/Комментировать
2020-10-13 09:31:59 የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በ3ዙር ተማሪዎቹን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገለፀ!

በኮሮና ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስጀመር ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተወጣጣ ኮሚቴ የሐዋሳ ዩንቨርስቲ አያደረገ ያለውን ዝግጅት ገምግሟል፡፡

ከግምገማው በኀላ በተሰጠ መግለጫ የሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን መቀበል በሚያስችለው ቁመና ላይ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ጠቅላላ አስተዳደር ሀላፊ አቶ ጌታቸው ተፈራ ገልጸዋል፡፡ ጥቂት ቀሪ ስራዎችን ባሉት ጊዜ ማጠናቀቅ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡

የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አያኖ በዳሳ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው በሦስት ዙር ተማሪዎችን ለመቀበል ማቀዱን ተናግረዋል፡፡

በዚህም በመጀመሪያ ዙር 5820 ተመራቂ ተማሪዎችን የሚቀበል ሲሆን ነባር እና አዳዲስ ተማሪዎችን በሁለተኛ እና ሦስተኛ ዙር ለመቀበል ታቅዶአል ይህም እስከ #ሚያዚያ ባለው ጊዜ ይሄዳል ብለዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የግንዛቤ ማስጨበጫ እንዲሁም ማስክ እና ሴኒታይዘር ያሉ ቁሳቁሶችን በበቂ ሁኔታ ለመስጠት ማዘጋጀቱንም ዶክተር አያኖ አረጋግጠዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የዪንቨርስቲው ቴክኖሎጂ ጊቢ ለለይቶ ማቆያነት እየተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡

ምንም እንኳን የሐዋሳ ዩንቨርስቲ ዝግጅቱን ቢያደርግም ትምህርት እንዲጀምር የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም እውቅና እስኪሰጠው እንደሚጠብቅ ተገልጿል፡፡

t.me/worldedunews
99 views06:31
Открыть/Комментировать
2020-10-12 21:26:12 Let us start on geography

Relative location, size and shape of Africa

Relative location
Africa is found to the:

 South of Europe
 Southwest of Asia
 South of the Mediterranean Sea
 West of the Indian Ocean
 East of the Atlantic Ocean
 East of the Atlantic Ocean
 Africa gets closest to Europe across the Strait of Gibraltar, which is about 22 kms wide
between Morocco and Spain.
 Africa gets closest to Asia across the Strait of Bab-el Mandab, which is about 40 kms wide.
 A narrow stretch of land called the Isthmus of Suez, which is cut into two by an artificial
canal called the Suez Canal, connects Africa with Asia.
 The implications of Africa’s elative location are
 Geographically Africa is accessible to almost all continents
 Socio economic and political relations are easily established
94 views18:26
Открыть/Комментировать
2020-10-12 20:35:10 ትምህርት ሲጀመር መማሪያ ክፍልና የማስተማሪያ መሣሪያዎች አጠቃቀም | Precautions to be taken in Class at the beginning of learning:-

1ኛ. ትምህርት ክፍሉ ያሉትን የመማሪያ ክፍሎች ለገጽ ለገጽ ትምህርት ሲደለድል አንድ ክፍለ ጊዜና ቀጣይ ክፍለ ጊዜ መካከል የማጽዳና የማናፋስ ሥራ የሚሰራበት ቢያንስ የአንድ ሰዓት ክፍተት እንዲኖር ማድረግ አለበት።

2ኛ. ለመምህሩ መንቀሳቀሻ የሚሆን ከመጻፊያ ሰሌዳና ከፊት ረድፍ በሚቀመጡ ተማሪዎች መካካል ቢንያስ የሶስት ሜትር ርቀት መኖር አለበት።

3ኛ. የተማሪዎቹ የወንበር አቀማመጥ 2 ሜትር አካላዊ ርቀት የጠበቀ መሆን አለበት፡፡

4ኛ. የመማሪያ ክፍሎች በርና መስኮት በመማር ማስተማር ወቅት ሁል ጊዜ ክፍት መሆን አለባቸው፡፡ መምህሩም በቂ የአየር ዝውውር መኖሩን ሳያረጋግጥ ማስተማር የለበትም።

5ኛ. ማንኛውም ወደመማሪያ ክፍል የሚገባ መምህርና ተማሪ ከመግባቱ በፊት እጁን በሳሙና በአግባቡ በተዘጋጀው መታጠቢያ ቦታ መታጠብና በመማሪያ ክፍል ውስጥም አፍና አፍንጫውን በማስክ የመሸፈን ግዴታ አለበት።

6ኛ. በመማሪያ ክፍል ውስጥ ምንም ዓይነት አካላዊ ቅርርብ እንዲኖር የሚያደርግ የቡድን ውይይት የተከለከለ ነው።

7ኛ. ማንኛውንም ተንቀሳቃሽ የማስተማሪያ መሣሪያ (ኤል ሲዲ፣ ፖይንተር፣ ዳስተር፣ ኮምፕዩተር…ወዘተ) በጸረ- ተዋህሳን ወይም በሌላ ቴክኖሎጂ ሳይጸዳ በእጅ መቀባበል የተከለከለ ነው።

8ኛ. በመማሪያ ክፍል ተገጥመው የሚገኙ ማንኛውንም የማስተማሪያ መሣሪያዎችን (ስማርት ቦርድ፣ ኤል ሲዲ፣…የመሳሰሉትን) ከተፈቀደለት ሰው በስተቀር ማጽዳትም ሆነ መነካካት ክልክል ነው።

9ኛ. የመማሪያ ክፍሎችን መዝጋትና መክፈት ለዚሁ በተቋሙ በተመደቡ ሠራተኞች ብቻ ማከናወን የግዴታ ሲሆን የእጅ ጓንት በማደድረግና ኬሚካል ማጽጃ በመጠቀም መዝጋትና መክፈት ይቻላል፡፡
@worldedunews
@worldedunews
@worldedunews
98 views17:35
Открыть/Комментировать