Получи случайную криптовалюту за регистрацию!

ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላለፈ መልዕክት ለክልላችን መምህራን፣የተማሪ ወላጆች፣ ባለሙያዎ | Educational news

ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተላለፈ መልዕክት

ለክልላችን መምህራን፣የተማሪ ወላጆች፣ ባለሙያዎችና አጋር አካላትና መላ ማህበረሰባችን በሙሉ!!

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሀገራችን ከተከሰተ መጋቢት 2012 ጀምሮ ት/ቤቶች ተዘግተው መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ትምህርት ቤቶችን እንደገና በመክፈት የመማር ማስተማር ስራውን ለማስቀጠል ሀገራዊ ስምምነት ስለተደረሰ ኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተቀመጡ ኘሮቶኮሎችን በትምህርት ቤቶች መተግበር የግድ የሚልበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ በዚህም መሰረት፡-

1ኛ.የክልላችን መምህራን፣ የተማሪ ወላጆች፣ ባለሙያዎች፣ አጋር አካላትና ጉዳዩ የሚመለከታችሁ በሙሉ እና በአጠቃላይ የክልላችን ህዝብ ልጆቻችሁ የሚማሩበት ት/ቤት የኮቪድ 19 መከላከል ኘሮቶኮሎችን ለመተግበር የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በጋራ በመረባረብ እንድትፈቱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ጥሪውን ያቀርባል፡:

2ኛ. ነባርም ሆነ አዲስ ተማሪዎች፣ የአካባቢው ት/ቤት በሚያወጣው ፣ ኘሮግራም መሰረት በእለቱ በመገኘት ትምህርት እንዲጀምሩ ፣ ወላጆች የበኩላቸውን ኃላፊነት እንድትወጡ እንጠይቃለን፡፡ የ2013 የትምህርት ዘመን በኮቪድ ተፅዕኖ ምክንያት የትምህርት ቀናት አጭር ሊሆኑ ስለሚችሉ አንድም ተማሪ ዘግይቶ ወደ ት/ቤት መግባት ከፍተኛ ጉዳት ያለው መሆኑን ተረድተን ሁላችንም የትምህርት መርሃ ግብሩን አክብረን ለመስራት እንረባረብ !!
ኮቪድን እየተከላከልን 2013 የትምህርት ዘመን ፣የሰላምና የስኬት እንዲሆንላችሁ ቢሮው ምኞቱን ይገልፃል!!
(የአብክመ ትምህርት ቢሮ)

Share join join join
@worldedunews
@worldedunews
@worldedunews