Получи случайную криптовалюту за регистрацию!

በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ጥቅምት 16 ትምህርት ይጀምራሉ! በኦሮሚያ ክ | Educational news

በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ጥቅምት 16 ትምህርት ይጀምራሉ!

በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማእረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ በሰጡት መግለጫ በክልሉ ከጥቅምት 16 ጀምሮ ተማሪዎች በሦስት ዙር ተከፍለው ትምህርት እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም በመጀመሪያ ዙር ጥቅምት 16 የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩ ይሆናል፣ በሁለተኛው ዙር ደግሞ ጥቅምት 30 የዞን በሁሉም ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምሩ ይሆናል ብለዋል፡፡

በሦስተኛው ዙር ልዩ ዞኖችና በፊንፊኔ ዙሪያ ያሉ ከተሞች ትምህርት ይጀምራሉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በክልሉ ከ33 ሺ በላይ አዳዲስ መማሪያ ክፍሎች መገንባታቸውን ያስታወሱት አቶ አዲሱ በዚህ ዓመት ከ11.5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን ለማስተማር መታቀዱን ገልጸዋል፡፡ (OBN)

@worldedunews
@worldedunews
@worldedunews