Получи случайную криптовалюту за регистрацию!

ከትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተሰጠ የሀዘን መግለጫ ................... | Ethiopian University መረጃ

ከትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

............................................................................

የትውልድ የእውቀት አባቶች ፣ የሀገር ተረካቢ ዜጎች መሃንዲሶች የሆኑ ትውልድ ለማፍራት ደፋ ቀና ሲሉ መንገድ ላይ የቀሩ መምህራን ህልፈተ ህይወታቸው ልብ ይሰብራል!

የመደ ወላቦ መምህራን እንደ ወጡ መቅረታቸው ሀዘኑ መራር ነው። ፈጣሪ ለነፍሳቸው ዘላለማዊ እረፍትን ይስጥልን !

በአደጋው ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና ላይ ለሚገኙ መምህራንም ፈጣሪ ምህረቱን ይስጣቸው!

አደጋው መላውን ህዝብ በተለይም ቅርባቸው የሆነው የትምህርቱን ማህበረሰብ እጅግ ያስደነገጠና ልብ የሚሰበር ለሙያ የተከፈለ መስዋዕትነት ነው።

ተማሪዎችን በእውቀት አንጸው ለመመለስ የወጡ መምህራን ወደቤተሰባቸው መመለስ ሳይችሉ በወጡበት በመቅረታቸው እጅግ አዝኛለሁ።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና ጓደኞቻቸው በሙሉ እንዲሁም ለመደ ወላቦ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ መጽናናትን እመኛለሁ።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ!
የትምህርት ሚኒስትር!